በእሳት የማይቃጠል ዘመናዊ ጡብ በአሶሳ ዞን ማረሚያ ቤቶች መምሪያ አስተዳድር ውስጥ በሚገኙ የህግ ታራሚዎች መመረቱ ተገለፀ ፤

በእሳት የማይቃጠል ዘመናዊ ጡብ በአሶሳ ዞን ማረሚያ ቤቶች መምሪያ አስተዳድር ውስጥ በሚገኙ የህግ ታራሚዎች መመረቱ ተገለፀ ፤
በእሳት የማይቃጠል ዘመናዊ ጡብ የህግ ታራሚዎች መመረቱን የገለፁት በአሶሳ ዞን ማረሚያ ቤቶች መምሪያ አስተዳድር ውስጥ ለሚገኙ የህግ ታራሚዎች የአካባቢ ንፅህ አጠባበቅ ዙሪያ ከአሶሳ ዩንቨርስቲ በመጡ ባለሙያዎች ለህግ ታራሚዎች ሥልጠና እየተሰጠ ባሉበት ወቅት ነው፡፡
በስልጠናው ላይ የግልና የአካባቢ ንፅህናቸውን ካልጠበቁ በሽታ አምጪ ባክቴሪያ ከአንዱ ወደ አንድኛው የመተላለፍ ዕድል እንደሚኖረው እና ሁሉም የህግ ታራሚ የግሉን እና የአካባቢውን ንፅህና መጠበቅ እንዳለባቸው ተገልፃል፡፡
የዞኑ ማረሚያ ቤት አስተዳደር በህግ ታራሚዎች የግልና የአካባቢ ንፅህ እንዲጠብቁና ብቁና ጠንካራ ዜጋ ሆነው ከማረሚያ ቤት ሲወጡ ከሚቀላቀሉት ማህበረሰብ ጋር የሰላ ጤናማ አገር ወዳድ ስሜት ተላብሰው እንዲወጡ በአትኩሮት እንደሚሰራ በስልጠናው መክፈቻ ላይ ተነግሯቸዋል፡፡
በአሶሳ ዞን ማረሚያ ቤቶች መምሪያ አስተዳድር ውስጥ ለሚገኙ የህግ ታራሚዎች ሙሉ ጠየንነታቸው ከመጠበቁ የተነሳ በአገኙት ስልጠና በእሳት የማይቃጠል ዘመናዊ ጡብ እያመረቱ በሚያገኙት ገቢ ለራሳቸው እና ለቤተሰቦቻቸው የገቢ ምንጭ እያገኙበት መሆኑን የዞኑ ማረሚያ ቤቶች መምሪያ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮማንደር ሸዋቀና ገርቢ ገለፀዋል፡፡
መረጃው በአሶሳ ማረሚያ ቤት የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮማንደር ሸዋቀና ገርቢ ነው፡፡