የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ የፍትህ አሰጣጥ ስርዓትን ማጠናከር እንደሚገባ የክልሉ ፍትህ ቢሮ ሃላፊ አቶ መሃመድ ሃሚድ ገለጹ።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ የፍትህ አሰጣጥ ስርዓትን ማጠናከር እንደሚገባ የክልሉ ፍትህ ቢሮ ሃላፊ አቶ መሃመድ ሃሚድ ገለጹ።

ቢሮው የፍትህ ተቋማትን የትራንስፎርሜሽን አተገባበር እውን ለማድረግ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪ ለዘርፉ ባለሙያዎች በግልገል በለስ ከተማ ስልጠና ሰጥቷል።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልልፍትህ ቢሮ ሃላፊ አቶ መሃመድ ሃሚድ በክልሉ ውስጥ የህግ የበላይነትን በዘላቂነት ለማረጋገጥ የፍትህ አሰጣጥ ስርዓትን ማጠናከር እንደሚገባ ገልጸዋል።

ተቋሙ ፍትህ እንዲረጋገጥ የዘርፉን ባለሙያዎች ክህሎት በማሳደግ ያለ ምክንያት የሚዘገዩ ጉዳዮችን በማስወገድ ዜጎችን ከመጉላላት መታደግ ላይ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ቢሮ ሃላፊው አክለው ተናግረዋል።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር መንግስቱ ላሎ በበኩላቸው፣ ለህብረተሰቡ ተደራሽና ፍትሃዊ የሆነ የፍትህ አገልግሎት ተጠቃሚ ለማድረግ የፍትህ ተቋማትን አሰራር ማዘመንና መደገፍ እንደሙገባ አብራርተዋል።

እንደ ሀገር የተጀመረውን የተጀመረውን የህግ የበላይነት ማረጋገጥ ተግባር እውን ለማድረግ የፍትህ አካላት አፈጻጸምን በህዝብ መድረክ መገምገም አለባቸው የሚለውን መርህ ለመተግበር እየተሰራ መሆኑን የተናገሩት ደግሞ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የምርመራ ዘርፍ ሃላፊ ምክትል ኮሚሽነር አምሳሉ ኢረና ናቸው።

በስልጠናው ላይ የተያዙና የተከሰሱ ሰዎች ሰብዓዊ መብት አያያዝ፣የወንጀለኛ መቅጫ ስነ ስርዓት እና የፍትህ ተቋማት የትራንስፎርሜሽን አተገባበር የሚሉ ሰነዶች ቀርበዋል።

የክልሉ ፍትህ ቢሮና ፖሊስ ኮሚሽን ከአሶሳ ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር በተሰጠው ስልጠና ውስጥ የሁሉም ወረዳ መርማሪ ፖሊሶችና አቃቢያነ ህጎች መገኘታቸውን ከዞኑ ኮሙኒኬሽን መምሪያ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።