በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ም/ፕሬዚዳንት አቶ መሃመድ አቡድ የተመራ የክልል ፍትህ ፎረም ቡድን አባላት ከአብራሞ ወረዳ ፍትህ ፎረም አካላት ጋር በወረዳዉ የፎረሙ የስራ እንቅስቃሴዎች ዙሪያ ዉይይት ተደረገ፤
የካቲት 19/2017ዓ/ም፤ አብራሞ) በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ም/ፕሬዚዳንት አቶ መሃመድ አቡድ የተመራ የክልል ፍትህ ፎረም ቡድን አባላት ከአብራሞ ወረዳ ፍትህ ፎረም አካላት ጋር በወረዳዉ የፎረሙ የ6 ወራት የዕቅድ አፈፃፀም ዙሪያ ተወያይተዋል።
የወረዳዉ ፍትህ ፎረም የዕቅድ አፈፃፀም መነሻ ረፖርት በፎረሙ አባል ቀርቦ ዉይይት ተደርጎበታል።
የጋራ እቅድ አቅዶ የጋራ የተጠናከረ የአፈፃፀም ሪፖርት ከማቅረብ አንፃር ክፍተት መኖሩን የዉይይት መድረኩን የመሩት የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ም/ፕሬዚዳንት አቶ መሃመድ አቡድ ጠቁመዉ ለዉይይት እንደመነሻ ለቀረበዉ ሪፖርት ለወረዳዉ ፎረም አባላት ምስጋናቸውን በማቅረብ በቀጣይ ለጉዳዩ የበለጠ ትኩረት ተሰጥቶት በጋራ ሊሰራ እንደሚገባ አስገንዝበዋል ።
ንቃተ ህግ ትምህርት አሰጣጥን በተመለከተ አብራሞ ወረዳ የሰዎች መግቢያ እና መዉጪያ ከመሆኑ ጋር በተያያዘ ለህገ ወጥ የሰዎች ዝዉዉር እና መሰል ወንጀሎች ተጋላጭ መሆኑን አቶ መሀመድ አቡድ አስታዉሰዉ እነዚህን ወንጀሎች ከመከላከል አኳያ ችግር ፈቺ ትምህርት ለህብረተሰቡ ተደራሽ ማድረግ እንደሚገባም በዉይይቱ አንስተዋል ።
በተከሳሽና በከሳሽ አለመቅረብ ምክንያት የተዘጉ መዝገቦች አለመኖራቸዉ የወረዳዉን የፎረም አካላት ተቀራርቦ መስራት ማሳያ መሆኑን አቶ መሃመድ አቡድ ከዉይይቱ መረዳታቸዉን ገልፀዉ የበለጠ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባም አስተያየታቸዉን ሰጥተዋል።
የመንግስትንና የህዝብን ጥቅም ከማስጠበቅ አንፃር የወረዳዉ ፍትህ ፎረም አካላት ቅንጅታዊ አሰራራቸዉን አጠናክረዉ በማስቀጠላቸዉ አፈፃፀማቸዉ የተሻለ ቢሆንም በየጊዜዉ የሚፈፀመዉን የመሬት ወረራ በማስቀረት በህብረተሰቡ ዘንድ ለሚነሱ የመልካም አስ/ር ችግሮች ፈጣንና ተገቢ ምላሽ ከመስጠት አንፃር ዉስንነቶች መኖራቸዉን፤ በደን ሀብት ላይ የሚደርሱ
ጉዳቶችን ቀድሞ ከመከላከልና ጉዳት አድራሾችን ይዞ ለህግ ከማቅረብ ጋር በተያያዘ አበረታች ጅምር ስራዎች ቢኖሩም ቀሪ ስራዎች መኖራቸዉ በዉይይቱ ተነስቶ በቀጣይ ትኩረት ሊሰጥ እንደሚገባ አቅጣጫ ተሰጥቷል።
በፎረሙ ዉይይት የተገኙት የአብራሞ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ባበክር ሃሚድ የወረዳዉን የፍትህ ፎረም የስራ እንቅስቃሴዎች ውጤታማነት ለማረጋገጥ ሁለንተናዊ ድጋፋቸዉን እንደሚያደርጉ ገልፀዉ የወረዳዉ ህዝብ በሰላም ወጥቶ በሰላም መግባት እንድችል በማድረግ እና ፍትሃዊ ተጠቃሚነቱን በማረጋገጥ ረገድ ከወረዳዉ ፍትህ አካላት ጋር ተቀራርቦ ለመስራት ቁርጠኛ መሆናቸዉን ገልፀዉ ቅንጅታዊ አሰራራቸዉን የበለጠ አጠናክረዉ በማስቀጠል በፍትህ ዘርፉ የሚስተዋለዉን የአገልግሎት አሰጣጥ ችግር ለመቅረፍ ትኩረት ሰጥተዉ ሊሰሩ እንደሚገባ አስተያየታቸዉን ሰጥተዋል።
የህብረተሰቡን የንቃተ ህግ ደረጃ በማሳደግ የወንጀል መከላከል አቅም እንድጎለብት ለማድረግ የተጀመሩ የንቃተ ህግ ትምህርት ስራዎች መሠረታዊ ችግሮችን መፍታት በሚችሉበት አግባብ ተጠናክረዉ ሊቀጥሉ እንደሚገባም የአብራሞ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ባበክር ሃሚድ አክለዉ ተናግረዋል።
የአሶሳ ዞን ፍትህ መምሪያ ሀላፊ አቶ ቁረሽ አጠይብ ፍትህ ፎረም ዋና አላማዉ የፍትህ አካላት በጋራ እየተገናኙ ስራዎቻቸዉን በጋራ በመገምገም እና ጠንካራ አፈፃፀሞችን በመለየት እና እዉቅና በመስጠት በክፍተቶች ላይ የተሻለ የማስፈፀሚያ ስልት በመቀየስ ለተሻ
