‎የሕግ ታራሚዎች የልማት ተሳትፎ እንዲኖራቸው እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት ተጠናክረው ይቀጥላሉ

‎የሕግ ታራሚዎች የልማት ተሳትፎ እንዲኖራቸው እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት ተጠናክረው ይቀጥላሉ

‎የአሶሳ ዞን ማረሚያ ቤት መምሪያ የአሶሳ ከተማ አህመድ ናስር ስቴድዬም  እና የከተማዉ የኮሪደር ሥራዎችን በህግ ታራሚዎች እየተሰራ መሆኑን ገለፀው ታራሚዎቹ የራሳቸውን አሻራ ለማሳረፍ እንድችሉ ዕድሉን ለሠጠቸዉ የተቋሙ አመራሮችና አጅበዎቸዉ የወሰዱዎቸውን የጥበቃ አባላቶችን በማመስገን ቀጣይነት እንድረዉ ጠይቋል ።

‎አሶሳ ፦ግንቦት 6/2018ዓ.ም

‎የአሶሳ ዞን ማረሚያ ቤት መምሪያ ኃላፊ ምክትል ኮሚሽነር አልቃሲም አወድ  ማረሚያ ተቋም የህግ ታራሚዎችን ሰባዓዊ መብቶችን በመጠበቅ በማረምና በማነፅ ሥራዎችን ጎን ለጎን ታራሚዎችን የሙያ ባለቤት እንድሆኑ ከተቋሙ ጎን ሆኖዉ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እያበረከቱ ለነበሩ ተቋማት፣የተቋመት አመራሮችና ሠረተኞች አመስግነዉ ይህ መልካም ተግባር የእነሡ መሆኑ ተገለፀ ።

‎በማረሚያ ቤት ቆይታቸው ታራሚዎችን ከማረምና ከማነጽ ሥራ ጎን ለጎን በተለያዩ የሙያ መስኮች እንዲሰለጥኑ እየተደረገ መሆኑንም ጠቁመዋል።

ታራሚዎች በማረሚያ ቆይታቸው የተለያዩ ሥልጠናዎች እንድያገኙ መደረጉ ‎መንግስት  ለዜጎች እየሰጠ ላለው ትኩረት ማሳያ መሆኑ አብራርተዋል ።

‎በከተማው ለሚሰሩ ማንኛውም የሙያ ሥራዎች ለታራሚዎች የሚሰጡ ድርጅቶች ካሉ ሥራው በጥራት ሠርተዉ እንደሚያስረግቡ ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገብተዋል ።

‎ተቋሙ እያስመዘገበ ያለው ውጤት  የአመራሮቹ እና የአባሎቻቸውን ሚና የማይተካ መሆን አብራርተው ።

‎ተቋሙ በእኩልነት ሁሉ ዜጋ በማረም  ለሀገር ግንባታ  ትልቅ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆን ገልጸዋል ።

‎ከተቋሙ ጎን ሆነው ለታራሚዎች እና ለአባላቱ የተለያዩ ትምህርቶች

‎ እንዲማሩ፣ ድጋፍ ስያደርግላቸዉ የቆዩት የአሶሳ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅን አመስግነዉ ታራሚዎቹ በገኙት ሙያ ተደራጅተው እንዲሠሩ፣ በተለያዩ የሙያ መስኮች የሥራ ዕድል እና የሥራ ላይ ሥልጠናዎች እንዲያገኙ፣ በጥፋታቸው ተፀፅተው ማኅበረሰቡን እንዲክሱና አምራች ዜጋ እንዲሆኑ ለማድረግ ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥርላቸዉ ቃል ገብተዋል ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *