

የአሶሳ ዞን ማረሚያ ቤቶች መምሪያ በስሩ የሚያስተዳድራቸው የህግ ታራሚዎች በሚያለሟቸው የመስኖ እና የመኸር የአገዳ ሰብሎች የኑሮ ውድነቱን በማቃለል እረገድ ትልቅ ሚና እናዳላቸው የአሶሳ ዞን ማረሚያ ቤቶች መምሪያ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮማንደር ሸዋቀና ገርቢ ገለፁ፡፡
የኑሮ ውድነቱ ተቀጣሪ ሰራተኞችን ብቻም ሳይሆን በተለያየ የግል ስራ ላይ የተሰማሩና በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ የከተማ ነዋሪዎችን የሚመለከት በመሆኑም የእነዚህን የህብረተሰብ ክፍሎች ችግር የሚያቃልል የአሶሳ ዞን ማረሚያ ቤቶች መምሪያ በስሩ የሚያስተዳድራቸው የህግ ታራሚዎች በሚያለሟቸው የመስኖ እና የመኸር የአገዳ ሰብሎች በከተማዋ ገበያ ቦታ እንዲሸጥ እና ማህበረሰቡ በኑሮ ውድነቱ መንግስትን ከማማረር ይልቅ ለመንግስት መፍትሄ አመንጪ ሀሳቦችን በመስጠት በቀጣይ በኑሮ ውድነቱ ላይ መንግስት ከሚወስደው የማስተካከያ እርምጃ እንዳለ ሆኖ በማረሚያ ቤቶች ስር የሚተዳደሩ የህግ ታራሚዎች በሚያለሟቸው የመስኖ እና የመኸር የአገዳ ሰብሎች የኑሮ ውድነቱን ከማረጋጋት አኳያ ትልቁን ድርሻ እየወሰደ እንደሚገኝ መንግስትም ሆነ የከተማዋ ነዋሪዎች እንዲረዱልን እንፈልጋለን ብለዋል፡፡
ማረሚያ ቤቱ የህዝቡን የኑሮ ውድነት ለማቃለል ከልቡ እስካሰበ ድረስም በራሱ የልማት ድርጅቶች አማካኝነት በሚያመርታቸው በቆሎ፣ ካሳባና የጡብ ምርቶች ላይ ትርጉም ያለው ቅናሽ ማድረግ በማድረግ የአካባቢው ማህበረሰብ ላይ የኑሮ ውድነቱን ከማረጋጋት አልፎ የህግ ታራሚዎች በሚያገኙት ገቢ ለቤተሰቦቻቸው እና ለራሳቸው የገቢ ምንጭ እየሆነ ይገኛል፡፡
መረጃው የአሶሳ ዞን ማረሚያ ቤቶች መምሪያ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮማንደር ሸዋቀና ገርቢ ነው፡፡
