የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ከUNHCR ጋር በመተባበር ከ17_18 /4/2017 ዓ.ም የሚቆይ የተያያዙ ስደተኞችንና የህግ ታራሚዎችን ሰባዓዊ መብት አያያዝን አስመልክቶ ለአሶሳ ዞን ማረሚያ ቤት መምሪያ ሀላፊዎች፣ለአባላትና ሰራተኞች የህግ ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ።

የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ከUNHCR ጋር በመተባበር ከ17_18 /4/2017 ዓ.ም የሚቆይ የተያያዙ ስደተኞችንና የህግ ታራሚዎችን ሰባዓዊ መብት አያያዝን አስመልክቶ ለአሶሳ ዞን ማረሚያ ቤት መምሪያ ሀላፊዎች፣ለአባላትና ሰራተኞች የህግ ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ።***

በስልጠናው ማስጀመሪያ ፕሮግራም ላይ የተገኙት የአሶሳ ዩኒቨርስቲ የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር ቁምላቸው አለሙ እንደገለፁት የማረሚያ ቤት ተቋም በፈረድ ቤት ተዕዛዝ የሚገቡ ታራሚዎችን ተቀብሎ በማረምና በማነፅ ዘረፈ ብዙ ተግባሮችን የሚያከናውን ስለሆነ የአባላቱን የህግ ግንዛቤ እውቀቱን በመገንባት የታራሚን ሰባዓዊ መብት አያያዝ እና አገልግሎት አሰጣጥ ተደራሽነቱን በማሻሻል እንዲሁም ተልዕኮውን በሚገባ ለመፈጸምና ህግና ደንብን ተከትሎ ሀላፊነትን ለመወጣትም ጭምረ ስልጠናው አስፈላጊ መሆኑን አብራርተዋል ።

የአሶሳ ዞን ማረሚያ ቤት መምሪያ ሀላፊ ምክትል ኮሚሽነር አህመድ አወድ በበኩላቸው እንደተናገሩት የአባላቱን ንቃተ ህግ ለማሳደግ አጫጭር ስልጠና ተዘጋጅቶ መሰጠቱ የታራሚ ሰባዓዊ መብት ተጠብቆ አገልግሎትን በተሟላ ሁኔታ ለመስጠት ስልጠናው ጉልህ ድረሻ እንደሚያበረክት አስገንዝበው ተቋሙ ታራሚን በማረምና በማነፅ ህግ አክባሪ፣ወንጀልን የሚፀየፍ ፣ሀገረ ወዳድና አምራች ዜጋ እንዲሁም የሙያ ባለቤት በማድረግ እየተሰራ መሆኑንም አክለው ገልፀዋል ።

ተሳታፊ ሰልጣኞች ትምህርቱን በንቃት ተከታትሎ ወደ ተግባር በመቀየር ህግና ስርዓቱን አስጠብቆ ተገልጋዩን ማህበረሰብ በማርካት ምቹና አስተማማኝ መደላድልን በመፈጠረ ብሎም አለም አቀፈ የሰባዓዊ መብት ድንጋጌዎችን በማክበረ የማረም ማነፁን ተግባር በሚፈልገው ደረጃ አሳድጎ ማስቀጠል እንደሚገባ አሰልጣኝ መምህራን ተናግረዋል ።

በመጨረሻም ይህንን ስልጠና ተሳታፊዎች በተግባር ለውጠው የተሰጣቸውን ሀላፊነት በአግባቡ ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ተተኪ ምክትል ኮሚሽነረ አልቃሲም አወድ ገልፀው፣ የቀጣይ የሰራ አቅጣጫና መመሪያን በመስጠት የስልጠናው መረሃ-ግብር የተጠናቀቀ መሆኑን የኮሚሽኑ ህዝብ ግንኙነት ከፍል ከስፍራው ዘግቧል ።