የአሶሳ ፖሊ ቴክኒክ ሙያ ማሠልጠኛ ተቋም በአሶሳ ዞን ለሚገኙ የህግ ታራሚዎች በአውቶመካኒክ ሙያ ዘርፍ ሥልጠና ልሠጥ ነው።
ግንቦት 13/2017*አሶሳ በአሶሳ ቴክኒክና ሙያ ማሠልጠኛ ኮሌጅ መምህራን መምህር አቢ ሽባበዉ እና መምህር እንድሪስ አራጋው ተነሣሽነት ለኮሌጁ በቀረቡት ፕሮፖዛል መሠረት ኮሌጁ በመምህራኑ በጎ ቅንነት በማድነቅ ከሌሎች ተግባራት በማስቀደም በአሶሳ ዞን ማረሚያ የሚገኙት ለ40 የህግ ታራሚዎች እና ለ5 የፖሊስ አባላት የአወቶ መካኒክ የሙያ ስልጠና ለመስጠት የክልሉ ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽንና የአሶሳ ሙያና ቴክኒክ ኮለጅ ክቡር አቶ ተመሰገ ሃዩ እና የክልሉ ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ኮሚሽነር ክቡር አቶ መንግስቱ ቴሶ ጋየጋራ ስምምነት አድርጓል ።የክልሉ ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር ክቡር አቶ መንግስቱ ቴሶ ተቋሙ ለማረሚያ ቤቶች በሚያደርገው በጉ አድራጎት በተቋሙ ስም ምስጋናቸውን በማቅረብ ለወደፊቱ የሚታደሪጉት ድጋፍ እንዳይለየን በማለት ተናግሯል ።

